መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2014-በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት በአንድ ጤና ጣቢያ የኮቪድ ምርመራ ካደረጉ 160 ሰዎች በ130 ያህሉ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ተባለ

በአዲስ አበባ በሚገኝ አንድ የጤና ጣቢያ ውስጥ በትላንትናው እለት የኮቪድ ምርመራ ካደረጉ 160 ሰዎች መካከል በ130 ያህሉ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረ ሃይል አስተባባሪ ዶክተር መብራቱ ማሴቦ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በትላንትናው እለት በተደረገ 10,016 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 2,323 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ገልፀዋል፡፡

በአንድ አካባቢ ላይ የሚታየው የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ጠቋሚ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ከሳምንታት በፊት የነበረውን የኮቪድ ምርመራ ውጤት ያነሱት ዶክተር መብራቱ በአንድ ቀን ከአንድ መዮ በታች በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የነበረ ሲሆን በያዝነው ሳምንት ግን ቁጥሩ አስጊ በሚባል ደረጃ መጨመሩን አንስተዋል፡፡

ይህ ቁጥር የሚያሳየው እንደ ሀገር የኮቪድ 19 ስርጭት ስጋት አሁን ላይ ከፍተኛ በመሆኑ ማንኛውም ሰው አጠራጣሪ ነገር ሲገጥመው መመርመር እና ክትባቱን መውሰድ እንዳለበት ጤና ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *