መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2014-እስራኤል አራተኛ ዙር የኮቪድ ክትባቶችን በመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር ልትሆን ትችላለች ተባለ

እስራኤል አዲሱን የኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ማዕበል ለመከላከል በዝግጅት ላይ ባለችበት ወቅት አራተኛውን የኮቪድ-19 ክትባት በመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር ለመሆን ማቀዷን ተናግራለች። የእስራኤል የወረርሽኝ መከላከል ባለሙያዎች እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ለሆኑ እና ለጤና ሰራተኞች አራተኛው ዙር ክትባት ቢወስዱ ይመከራል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት እቅዱን በደስታ ተቀብለው ባለሥልጣናቱ መዘጋጀት እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል። በትላንትናው እለት በእስራኤል በኦሚክሮን ዝርያ የመጀመሪያ ሞት የተመዘገበ ሲሆን ቢያንስ 340 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

አራተኛ ዙር ክትባትን ለመስጠት ግን የከፍተኛ የጤና ባለስልጣናት ይሁንታ ይፋልጋል ። የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኔት ጽህፈት ቤት እንደገለጸው የአራተኛው ዙር ክትባት ቢያንስ ሶስተኛው ዙር ከተወሰደ ከአራት ወራት በኋላ ለሰዎች እንደሚሰጥ ይፋ አድርጓል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *