መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2014-የሊቢያ ፓርላማ በሀገሪቱ አርብ ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ማከናወን የማይቻል ነው ሲል አስታወቀ

የሊቢያን የምርጫ ሂደት የሚቆጣጠረዉ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ኮሚቴ እንደታቀደው በሁለት ቀናት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የሀገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ የማይቻል ነዉ ሲል አስታዉቋል፡፡የቴክኒካል፣ የፍትህ እና የፀጥታ ሪፖርቶችን ካማከርን በኋላ በምርጫ ህጉ በተደነገገውን መሰረት የፊታችን አርብ ምርጫ ማካሄድ የማይቻል መሆኑን እናሳውቃችኋለን ሲል የኮሚቴው ሰብሳቢ ተለዋጭ ቀን ሳይሰጥ ለምክር ቤቱ ኃላፊ ደብዳቤ ጽፈዋል።

በአል ሃዲ አል-ሳጊር የተላከው ደብዳቤ የሊቢያ ከፍተኛ ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን መሪ በታህሳስ 2020 በወጣው ሰነድ ላይ የአስመራጭ ኮሚቴዎች በአገር አቀፍ ደረጃ የመጨረሻ የእጩዎችን ዝርዝር ሳይሰይሙ እንዲፈርሱ ካዘዘ በኋላ ይፋ የሆነ ደብዳቤ ነው ። በምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግን የመጀመሪያ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎች አርብ ይካሄዳል ይላል።

የኮሚቴው ደብዳቤ ምርጫው እንደታቀደው እንደማይቀጥል የሚያመለክት ሲሆን በተጨማሪም የፓርላማ አካሉ እና የምርጫ ኮሚሽኑ ምርጫውን በእርግጠኝነት ለማራዘም ሃላፊነት ያለው ማን ነው በሚለው ላይ አለመግባባት መፈጠሩን አመላካች ሆኗል፡፡ምርጫው በሊቢያ ወደ ነበረበት መረጋጋት ለመመለስ ያለመ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፍ ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *