መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2014-የሚካሄደዉ አገራዊ ዉይይት ከአሸባሪዎች ጋር እንዳልሆነ ይታወቅ ሲል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ድኤታ ከበደ ዴሲሳ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ሊደረግ የታሰበው አገራዊ ምክክር አሸባሪ በመባል ከታፈረጁት ቡድኖች ጋር እንዳልሆነ ተናግረዋል ።

ምክክሩ እየተደረገ ከሚገኘው ጦርነት ጋር ተያይዞ ለድርድር የታሰበ አለመሆኑን እና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላትን ያካተተ እንደሚሆን ተናግረዋል ። አያይዘውም ምክክሩ ሀገረ መንግስት ግንባታውን ለማጠናከር እንዲሁም ሀገራዊ መግባባትን ለማምጣት እንደሚረዳም ሚኒስቴር ደኤታው ገልጸዋል ።

በመግለጫው መንግስት አሁንም ለሰላም በሩ ክፍት መሆኑን አንስተዋል። ነገርግን ሊካሄድ የታሰበው ሀገራዊ ምክክር ከግለሰቦች እና በአሸባሪነት ከታወጁ አካላት ጋር እንደማይሆን ሚኒስትር ደኤታዉ አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *