መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2014-በጅማ ከተማ ሀሰተኛ የመሬት ማረጋገጫ ካርታን ህጋዊ አስመስለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ አራት መሀንዲሶች በእስራት ተቀጡ

የጅማ ከተማ መስተዳድር አራት የማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች ሀሰተኛ የመሬት ቦታ ማረጋገጫ ካርታን ህጋዊ አስመስለው በመስጠት ሲያጭበረብሩ የነበሩ አራት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን አስታዉቋል፡፡

ግለሰቦች አህመድ ያሲን፣ኢብራሂም ታቦ፣ይሳቅ ሱልጣን እና ሙኒክ ዝናቡ የተባሉ የጅማ ከተማ የማዘጋጃ ቤት መሀንዲሶች ናቸው። ለተለያዩ ግለሰቦች ሀስተኛ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ህጋዊ አስመስለው በመስጠት በህጋዊ የተያዘ የመሬት ይዞታ ላይ ሁከት እንዲፈጠር እና ለመንግስት ገቢ መሆን ያለበት በማስቀረት በፈጸሙት የማጭበርበር ወንጀል መከሰሳቸውን የጅማ ከተማ ወረዳ ሁለት የሙስና እና የመንግስት ገቢዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መርማሪ ዋና ሳጅን መንበሩ ይተና በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረት አንደኛ ተከሳሽ አህመድ ያሲን ሁለት አመት ከ9 ወር እስራት እና በአራት ሺ ብር መቀጮ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ኢብራሂም ያሲን ሁለት አመት ከሶስት ወር እስራት እና በ3 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

በተጨማሪም ሶስተኛ ተከሳሽ ሙኒክ ዝናቡ ሁለት አመት ከሶስት ወር እና አራት ሺ ብር መቀጮ እንዲሁም አራተኛ ተከሳሽ ይሳቅ ሱልጣን በሶስት አመት እስር እንዲቀጣ መወሱን ዋና ሳጅን መንበሩ ይተና ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *