መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 14፤2014-የዮቴክ ሪል ስቴት ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አደረጉ !!

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ ስያሜ ዮቴክ ሪል ስቴት እየተባለ የሚጠራ አከባቢ ነዋሪዎች በጋራ በመሆን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል ፡፡

ሁለት መቶ የሚጠጉት ነዋሪዎች ባሰባሰቡት ገንዘብ አማካይነት በትላንትናው እለት ቆሬ በሚገኘው የመከላከያ ማሰልጠኛ ዋር ኮሌጅ ተገኝተው ለጦር ቁስለኞች የምሳ ማብላት መረሃ ግብር ማድረጋቸውን ብስራት ሬድዮ ስፍራው ላይ ተገኝቶ ተመልክቷል ፡፡

ነዋሪዎች ለጦር ቁስለኞቹ ምሳ የማብላት መረሃ ግብር ከማድረጋቸው ባሻገር የ 4 መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ እንዳደረጉ አስተባባሪው አቶ ፀጋዬ ቸሩ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ፡፡

በማገገሚያ ስፍራው ላይ የሚገኙት የጦር ቁስለኞች ከራስ ህይወት በላይ የሀገርን ክብር አስቀድመው ዋጋ የከፈሉ ናቸው ያሉን የመከላከያ ማሰልጠኛ ዋር ኮሌጅ ምክትል ሃላፊው ኮ/ል አውግቼው ፍቃደ ሲሆኑ ይህ መሰሉ እንቅስቃሴ ለመከላከያ ሰራዊቱ ትልቅ የሞራል ስንቅ የሚሆን ነው ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ድጋፉን ያደረጉት የዮቴክ ሪል ስቴት ነዋሪዎች በበኩላቸው መሰሉን ድጋፍ በሚቀጥሉትም ጊዜያትም በማድረግ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

ናትናኤል ሀብታሙ !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *