መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 15፤2014-በቦረና ዞን በደረሰ የድርቅ አደጋ ከ180 ሺ በላይ ከብቶች መሞታቸዉ ተነገረ፤ከብቶችን ለመታደግ የሚደረገው ጥረት አዳጋች መሆኑ ተጠቁሟል

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ሳቢያ ለተፈጠረው የድርቅ አደጋ በትላንትናው እለት የገቢ ማሰባሰቢያ መረሀግብር ተከናውኗል፡፡በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የቦረና ተወላጅ ማህበር አሰባሳቢነት በተካሄደው መረሀግብርም ከ6.3 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የእርዳታው አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ አቶ ኤልያስ ጉዬ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በዝናብ እጥረት ምክንያ ድርቅ የተፈጠረባቸው አካባዎች ቦረና፣ ምስራቅ ጉጂ ፣ ከረዩ እና ከፊል ባሌ ዞኖች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ዞኖች መካከል በቦረና ዞን የደረሰው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት የእርዳታው አስተባባሪ አቶ ኤልያስ ባጋጠመው ድርቅ ከ300 ሺ በላይ አባወራዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺ በላይ ከብቶች መሞታውን ጠቁመዋል፡፡ አያዘውም አሁን ላይ ትኩረታችን ህይወት ለማትረፍ እንጂ ከብቶችን ለማዳን የሚደረገው ጥረት አስቸጋሪ መሆኑ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ሁለት የዝናብ ወቅቶች ቢኖሩም በነዚህ ወቅቶች 70 በመቶ በላይ የሚሆነው የዝናብ መጠን አለመዝነቡ ተነግሯል፡፡በቦረና ዞን 13 ወረዳዎች ያሉ ሲሆን ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን በላይ ህዝብ በአካባበዊዉ ይኖራል፡፡በተጨማሪም ከ6.8 ሚሊየን በላይ የከብቶች በዞኑም ይገኛሉ፡፡

የቦረና ዞን የአርብቶ አደር አካባቢዎች መሠረታዊ የአኗኗር ዘይቤ የሚከተል ሲሆን ከእንስሳት ጋር የተቆራኘም ነው፡፡በእነዚህ አካባቢዎች የሀብት መጠን የሚለካዉ በገንዘብ ብዛት ሳይሆን በከብቶች ብዛት ነው፡፡ የእርዳታ አስተባባሪዎቹም አሁንም ለወገን ደረሽ ወገን በመሆኑ ለመለው ኢትዮጵያውያን የድጋፍ ጥሪ አድርገዋል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *