መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 20፤2014-በደብረ ማርቆስ ከተማ ሠርግ ፣ተስካር እና መሠል ድግሶች በጊዜያዊነት ታገደ

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሠርግ ፣ተስካር እና መሠል የድግስ ፕሮግራሞች በጊዜያዊነት የታገደ መሆኑን የኮማንድ ፖስት አባል እና የደብረ ማርቆስ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ባንተአምላክ ካሳሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አሁን ካለው የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ችግር አኳያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በሚገኙበት ሁኔታ እና ለሀገራቸው ሲሉ መስዋትነትን የሚከፍሉ ወንድሞቻችን እንዲሁም በሚሊየን የሚቆጠር የንበረት ውድመት አኳያ ሰርግ እና አላስፈላጊ የሀብት ብክነትን ለመከላከል ታስቦ በጊዜያዊነት ሰርግ ፣ተስካር እና መሠል ፕሮግራሞች መታገዳቸውን ኮማንደሩ ገልፀዋል።

በሌላም በኩል በርካታ ህዝብ ተፈናቅሎ እያለ የተትረፈረፈ ድግስ ደግሶ መዝፈን እና መደለቅ ለሞራል፣ ለሀይማኖትም ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ሰርግ ለመሰረግ እና ተያያዥ ፕሮግራሞች ለማድረግ የተዘጋጁ የህብረተሰብ ክፍሎች በክልሉ ለተፈናቀሉ እና ለጥምር ሀይሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ፡፡

በልዩ ሁኔታ መጋባት የሚፈልጉ ለኮማንድ ፖስቱ ጥያቄ አቅርበው በማስፈቀድ ጋብቻው ከሰርግ ዝግጅት ውጭ እንዲፈፀም የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል። ይህንን ክልከላ ተላልፎ ጋብቻም ሆነ ተስካር እንዲወጣ የሚፈጽም እና የሚያስፈፅም የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አስፈፃሚ ግብረሀይሉ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮማንደር ባንተአምላክ ካሳሁን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *