መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 20፤2014-ኢንዶኔዥያ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ የጣለችውን እገዳ አነሳች

በላየን አየር መንገድ 189 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት አደጋ በ2018 ማጋጠሙን ተከትሎ ኢንዶኔዥያ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ እገዳ መጣሏ ይታወሳል።በላይን እና በኢትዮጲያ አየር መንገድ 737 ማክስ ላይ ከባድ አደጋ ከደረሰ በኃላ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአውሮፕላኑ አምራች ምርት እንዳይበር ተደርጓል።

ሰኞ እለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እገዳውን በማንሳት በየካቲት ወር በረራውን እንደሚቀጥል አስታውቋል።ከ180 በላይ ሀገራት 737 ማክስ አውሮፕላንን መጠቀም የፈቀዱ ሲሆን አውስትራሊያ ፣ጃፓን፣ ማሌዥያ እና ሲንጋፖር የጣሉትን እገዳ አንስተዋል።

የኢንዶኔዥያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ተቆጣጣሪዎች በአውሮፕላኑ ስርዓት ላይ የተደረገውን ለውጥ በመፈተሽ እገዳው መነሳቱን ገልጿል።በመግለጫው አየር መንገዶች 737 ማክስን እንደገና ከማብረር በፊት የአየር ብቁነት መመሪያዎችን በመከተል አውሮፕላኖቻቸውን መመርመር እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *