መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 22፤2014-በደብረብርሃን ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑ ተነገረ

ሰሜን ወሎ እና ደቡብ ወሎ በሽብርተኛው ህወኃት ስር የነበሩ ወረዳዎች እና ከተሞች በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በጥምር ጦሩ አማካኝነት ነፃ መውጣታቸውን ተከትሎ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች መመለሳቸውን ቀጥለዋል።ከዚህ ቀደም በደብረ ብርሀን ከተማ የነበሩ ተፈናቃዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን በደብረ ብርሀን ከተማ ሰላም እና ደህንነት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በከተማው ከተፈናቃዎች ተመሳስለው የገቡ ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር በማዋል የምርመራ ሂደት እየተጣራ በኮማንድ ፖስቱ ውሳኔ እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከ90 በላይ ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ወደ 30 የሚሆኑት በልዩ ሁኔታ የክስ መዝገባቸው እየተጣራ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥሪ ተደርጓላቸው ወደ ከተማው የሚመጡ ዲያስፖራዎች ለመቀበል የፀጥታ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እየተደረገ መሆኑን በተጨማሪም በቀጣይ የሚከበሩ በዓላትን ታሳቢ በማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ሀላፊወ ገልፀዋል ፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *