መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 22፤2014-የቀድሞ የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ከታሊባን የሸሸበት ቅጽበት ላይ ማብራሪያ ሰጡ

የአፍጋኒስታን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ታሊባን ስልጣን ሊቆጣጠር እየተቃረበ ሲመጣ ሀገራቸውን ለቀው ለመውጣት ያደረጉት ውሳኔ ዋና ከተማዋ ካቡል እንዳትወድም አድርጓል ሲሉ ተሟግተዋል።አሽራፍ ጋኒ በኦገስት 15 ከእንቅልፌ ስነቃ በአፍጋኒስታን የመጨረሻ ቀኔ ነበረ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ከሀገር መዉጣቴን የተረዳሁት እኔን ያሳፈረ አዉሮፕላን ከካቡል ከተማ ሲወጣ ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል።በወቅቱ ሀገሪቱን በአስጨናቂ ወቅት ከድተዉ ወጥተዋል የሚል ከፍተኛ ትችትና ክስ ቀርቦባቸዉ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በአሁን ወቅት አሽራፍ ጋኒ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ይገኛሉ።

ከሀገር የወጡበት ቀን ሲያስታዉሱ በማለዳ የታሊባን ተዋጊዎች ወደ ካቡል ላለመግባት ተስማምተው ነበር ፤ከሁለት ሰዓታት በኋላ ግን ይህ ስምምነት ፈረሰ ሲሉም ተናግረዋል፡፡ጋኒ ባለቤታቸዉን ጨምሮ ቅርብ ከሚሏቸዉ ሰዎች ጋር ካቡልን ለቀው ለመዉጣት ከብዙ ማቅማማት በኃላ መስማማታቸዉን ገልጸዋል፡፡በአራት መኪና ገንዘብ ይዘዉ ወጥተዋል መባላቸዉን በማስተባበል ከሀገሬ ገንዘብ አልዘረፍኩም ብለዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *