መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 22፤2014-የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ ፕሬዝደንት ፓርክ ለአምስት ዓመታት ከተጠጋ እስራት በኋላ ነፃ ወጣች

የቀድሞዋ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ፓርክ ጊዩን ሃይ በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአምስት አመት ገደማ ከተጠጋ የእስር ጊዜ በኃላ ከእስር ቤት የተለቀቁ ሲሆን በመጋቢት ከሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት ምንም ዓይነት ሚና ትጫወታለህ የሚለው ከወዲሁ ክርክር አስነስቷል።የ69 ዓመቷ ፓርክ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠች የመጀመሪያዋ የደቡብ ኮርያ መሪ ነበረች።

የሳምሰንግ እና ሎቴ ሁለት ዋና ስራ አስፈጻሚዎችን ለእስር ከዳረገዉ የምዝበራ ቅሌት ጋር ስሟ ተያይዞ ለእስር መዳረጓ ይታወሳል፡፡ፓርክ በእስር ላይ ካሉ ጓደኛዋ ጋር በመመሳጠር በአስር ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከኩባንያዎቹ በመቀበል ለጓደኛዋ ቤተሰብ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች፡፡

የወቅቱ የደቡብ ኮርያ ፕሬዝዳንት ሙን ጄ ኢን የጤና ሁኔታዋን እያሽቆለቆለ መምጣቱን በመጥቀስ እና ያለፈውን አሳዛኝ ታሪክ ለማሸነፍ እንዲሁም ብሄራዊ አንድነትን ለማጎልበት ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ ባለፈው ሳምንት ለፓርክ ልዩ ይቅርታ መስጠታቸዉ ይታወሳል፡፡የማረሚያ ባለስልጣናት እኩለ ለሊት ላይ የይቅርታ ደብዳቤ ካደረሱ በኋላ ፓርክ ካለፈው ወር ጀምሮ ለህክምና ከቆየችበት ሴኡል ሆስፒታል ስትወጣ የሚያሳይ ቪዲዮ በስፍት ተሰራጭቷል፡፡

የቀድሞ የደቡብ ኮርያ ወታደራዊ ገዥ ልጅ የሆነችው ፓርክ በተሰጣት ይቅርታ ዙሪያ ላይ አስተያየት ከመስጠት ብትቆጠብም ጠበቃዋ ግን ፕሬዝዳንት ሙን ጠንካራ ውሳኔ ስላደረገ አመስግነዋል፡፡ፓርክ ከእስር የተለቀቀችበት ወቅት የቀድሞ ፓርቲዋ፣ የወቅቱ ተቃዋሚ ወግ አጥባቂዉ የህዝቦች ሃይል ፓርቲ እና የፕሬዝዳንት ሙን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ለፕሬዚዳንትነት ውድድር ላይ ባሉበት ጊዜ ነው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *