መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 25፤2014-በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ከባድ የእሳት አደጋ መድረሱን ተከትሎ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ በደረሰ ከባድ የእሳት ቃጠሎ የሀገሪቱን ፓርላማ ህንጻን ክፉኛ ማዉደሙን ተከትሎ አንድ ሰው በቁጥጥር ስር ውሏል።የፖሊስ ቃል አቀባይ ግለሰቡ ቃጠሎ በማስነሳት፣ ቤት በመስበር እና በስርቆት ወንጀል ክስ ቀርቦበት እንደነበር በመግለጽ በነገዉ እለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተነግሯል።

የእሳት አደጋ ተከላካዮች እሳቱን ለማጥፋት ለሰዓታት ርብርብ ሲያደርጉ ቆይተዋል።ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የፓርላማው ስራ እንደሚቀጥል ቃል በመግባት አደጋዉን “አሰቃቂ እና አውዳሚ ክስተት” ሲሉ ጠርተዉታል።በትላንትናዉ እለት ከስፍራው የሚወጡ ምስሎች እንዳመላከቱት ከህንጻው ጣሪያ ላይ ከፍተኛ የእሳት ነበልባል ሰማዩን በጥቁር ጭስ ሲሸፍን ማስተዋል ተችሏል፡፡

የመንግስት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት እሳቱ በሦስተኛ ፎቅ ቢሮዎች ላይ በመነሳት በፍጥነት ወደ ብሄራዊ ምክር ቤት (የፓርላማው የታችኛው ምክር ቤት) ክፍል መዛመቱን ተናግረዋል፡፡ፓርላማው በአሁኑ ጊዜ በበዓል ምክንያት ስብሰባ እየተከናወነበት አይደለም፣ በአደጋዉ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *