መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 25፤2014-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሸባሪውና የትግራይ ቡድን በፈጸመው ወረራና በከተማዋ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን ተከትሎ አቋርጦት የነበረውን የላሊበላ በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል።

ወራሪውና አሸባሪው ቡድን በወገን ጦር ከባድ ምት ተቀጥቅጦ አካባቢውን ሲለቅ የላሊበላ አየር ማረፊያን ውደመትና ዘረፋ ማድረሱን መዘገባችን ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም ዘረፋና ውድመት የደረሰበትን የላሊበላ አየር ማረፊያ በአፋጣኝ አስተካክሎ ወደ ሥራ እንዲመለስ እንደሚያደርግ ገልፆ ነበር።

የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዳግም ለማነቃቃት እና በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የሚከበረውን ታላቁን የልደት በዓል ለማክበር መንግሥት በወሰደው እርምጃ አየር መንገዱ በአፋጣኝ ተጠግኖ ለአገልግሎት ብቁ ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *