መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 26፤2014-የገናን በዓል ከቤታቸው የተፈናቀሉትን በማሰብ ልናከብረው ይገባል ስትል የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገለፀች

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ወቅታዊ ችግሮች ተወግደው ለመኖርና ከመጥፎ ስራዎች ለመራቅ መፀለይ እንዲሁም ሁሉም ሰው በአብሮነት በአንድ መንፈስ ሊቆም ይገባል ሲሉ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ዛሬ ባስተለፏት መልዕክት ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ሰላም የደፈርሰ ቢሆንም ፈጣሪ በቃ ብሎ ሰላምን እንዲሰጠን ከቁጣ እና ከጥላቻ መንፈስ በመራቅ የይቅር ባይ መንፈስ ሊኖረን ይገባል መባሉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

አያይዘውም ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ፤ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። “በዓሉን ስናከብር ከቤታቸው የተፈናቀሉትን ህሙማን ፣ ታራሚዎችን እንዲሁም በተለያየ የስራ መስክ ሀገራችሁን የምታገለግሉ ሁሉ እንኳን ለልደት በዓሉ በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ ገልጸዋል።

ኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *