መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 27፤2014-ቻይና ሩም የተሰኘውን የአልኮል መጠጥ ወደ ሀገር እንዳይገባ እገዳ ብትጥልም ታይዋን 20ሺ ጠርሙስ መጠጡን ከሊቱዌኒያ ገዛች

አንድ የታይዋን ኩባንያ 20,400 ጠርሙስ ሩም የተሰኘ የአልኮል መጠጥ መግዛቱን ያስታወቀ ሲሆን ቻይና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ከልክላ ነበር፡፡ ቤጂንግ ከባልቲክ ሀገር ከሆነችዉ ሊቱዌኒያ ጋር በዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ትገኛለች፡፡የቻይና የጉምሩክ በዚሁ ግዢ ዙሪያ አስተያየት ለመስጠት ከፋክስ የመረጃ ምንጫ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጠጥቧል፡፡

የመንግስት ንብረት የሆነው የታይዋን ትንባሆ እና አረቄ ኮርፖሬሽን አልኮሉን ከኤምቪ ግሩፕ ከተሰኘ አምራች የገዛዉ የቻይና ጉምሩክ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ፍቃድ መከልከሉን ካሳወቀ በኋላ መሆኑ ተሰምቷል፡፡በትክክለኛው ጊዜ ሩም የተሰኘዉን መጠን ገዝተናል ስትል የተናገረችዉ ታይዋን “ሊቱዌኒያ ትደግፈናለች እኛም ሊትዌኒያን እንደግፋለን ስትል አስታዉቃለች፡፡

ታይዋን በሊቱዌኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያስፈጽም ቢሮ ከከፈተችበት ከህዳር ወር ጀምሮ ቻይና እና ሊትዌኒያ ዉዝግብ ዉስጥ ይገኛሉ፡፡ ድርጊቱ የአንድ ቻይናን መርህ ይጥሳል ታይዋን የራሴ ግዛት ናት ስትለ ቤጂንግ ትናገራለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *