መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 28፤2014-በዲፕሎማት ለውጥ ኢትዮጵያ አቋሟን እንደማትቀይር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ

የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ሳምታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ አምባሳደር ዲና የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ አምባሳደር ፌልትማን ከስልጣን ሊለቁ ነዉ በመባሉ ኢትዮጵያ የምትቀይረው አቋም እንደሌለ አምባሳደሩ አስታውቀዋል።

በጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ምላሽ የሰጡት አምባሳደሩ በዲፕሎማት ለውጥ ኢትዮጵያ አቋሟን እንደማትቀይር ለጋዜጠኞች አብራርተዋል ።

በተጨማሪም በሱዳን ያለን አለመረጋጋት ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የሚደረግ ጣልቃገብነትን ኢትዮጵያ እንደማትደግፍ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል ።

በሱዳን ካለዉ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አምባሳደሩ እንደተናገሩት ሱዳን ችግሩን ለመፍታት አቅሙ እንዳላት ኢትዮጵያ እንደምታምን ተናግረዉ የሚደረግ ማንኛውም ጣልቃገብነትን እንደማትደግፍ በመግለጫቸው አንስተዋል።

አክለዉም አምባሳደሩ በሳዑዲዓረቢያ በእስር የሚገኙ ዜጎችን ወደሀገር ለመመለስ ዝግጅቶች እየተድጉ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።

አምባሳደር ዲና አያይዘውም በተያዘው አዲሱ የፈረንጆች አመትም የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እና ነጻነትን ለማስከበር እንደሚሰራ ጨምረው በመግለጫቸዉ አንስተዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *