መደበኛ ያልሆነ

ጥር 2፤2014-በካዛኪስታን በተከሰተዉ ሁከትና ብጥብጥ ቢያንስ ከ160 በላይ ሰዎች ተገደሉ

ካለፈው ሳምንት አንስቶ የመካከለኛው እስያ ትልቋን ሀገር በሆነችዉ ካዛክስታን ውስጥ የተፈጠረዉ ሁከትና ብጥብጥ ከ160 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ5,000 በላይ ሰዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እሁድ እለት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጠዉ መግለጫ እንደገለፀው በሁከቱ ወደ 198 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የንብረት ውድመት መድረሱን አስታዉቋል፡፡

በነዳጅ ዋጋ ንረት ምክንያት የተቀሰቀሰው ሰልፍ በመላ ሀገሪቱ በመቀጣጠሉ ወደ ከፍተኛ ግርግር እንዲቀየር ምክንያት ሆኗል፡፡ካዛኪስታንን ለሶስት አስርት አመታት የመሩት እና አሁንም ከፍተኛ ተፅእኖን እንዳላቸዉ የሚታመኑት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኑርሱልታን ናዛርባዬቭ ላይ እና የሀገረቱ መንግስት ላይ ቅሬታቸውን ሰልፈኞች አሰምተዋል፡፡

በሁከቱ ከ100 በላይ የንግድ ድርጅቶችና ባንኮች ላይ ጥቃትና ዝርፊያ የተፈጸመ ሲሆን 400 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል፡፡ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 164 ሰዎች በሁከት መሞታቸውን የሩስያ የዜና ወኪል ስፑትኒክ የካዛኪስታንን የጤና ሚኒስቴር ጠቅሶ ዘግቧል።

በካዛክስታን ዋና ከተማ በሆነችው በአልማቲ 103 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ይህም በመዲናዋ ሁከቱ የከፋ እንደነበር አመላክቷል።ባለፈው ሳምንት ሩሲያን ጨምሮ ከሌሎች ሀገራት የተውጣጡ ወታደሮች ወደ ካዛክስታን በማምራት መረጋጋት እንዲፈጠር እየሰሩ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *