መደበኛ ያልሆነ

ጥር 3፤2014-በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ሰሜን ኮርያ ባልስቲክ ሚሳኤል አስወነጨፈች

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ጠዋት ባልስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏ የተሰማ ሲሆን ፒዮንግያንግ የሃይፐርሶኒክ የጦር መሳሪያ ሙከራ ባደረገች ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይህንን ሙከራ መፈጸሟን ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ አስታዉቀዋል፡፡ዛሬ ጠዋት ሰሜን ኮሪያ የባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራን ከምስራቅ ባህር አቅጣጫ ማድረጓን የደቡብ ኮርያ ጦር ሰራዊት መገኘቱን የሴኡል የሰራተኞች የጋራ ሃላፊዎች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ሰሜን ኮርያ ሙከራ መፈጸሟን በጃፓን የባህር ዳርቻ ጠባቂዎችም ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ባለስቲክ ሚሳኤል የመሰለ ነገር መተኮሱን ተናግረዋል፡፡በቶኪዮ የሚገኘው የመንግስት የዜና ኤጀንሲ የኪዮዶ በሙከራዉ ዙሪያ ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ማስወንጨፏን መቀጠሏ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡አስቸኳይ ስብሰባ ያካሄደው የደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሙከራዉ ማዘኑን ገልጿል ሲል የፕሬዚዳንቱ ሰማያዊ ሀውስ አስታዉቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ እና ጃፓንን ጨምሮ ስድስት ሀገራት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቀችዉ ሰሜን ኮሪያ አስፈሪ ድርጊቶቿን እንድታቆም በመጠየቅ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ዝግ መወያየታቸዉ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *