መደበኛ ያልሆነ

ጥር 3፤2014-በአዲስ አበባ በተያዘው ዓመት ማብቂያ ድረስ 25 መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ይደረጋሉ ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት 6 ወራት የእቅዱን 91 በመቶ የግንባታ ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን የጥገና እና መሰል ስራዎችን ደግሞ ከዕቅድ በላይ ማሳካቱ ገልጿል። በዚሁ ጊዜ ውስጥ ከ15 በላይ የመልካም አስተዳደር ችግር የነበረባቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ እንደተቻለ የባላስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እዮሱ ሰለሞን ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በከተማዋ ከ100 በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥም በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ 25 መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

ባለፉት 6 ወራት የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ቢሆንም በቀጣይ ግማሽ ዓመት ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ርብርብ እንደሚደረግ አንስተዋል።ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበሩ በርካታ የአስፋልት መንገዶች በቀንና በማታ ጥገና ተደርጎላቸው ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠር መደረጉን ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት የታዩ የወሰን ማስከበር፣ የግብዓት እጥረት እና የበጀት ውስንነት የመሳሰሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተነጋግሮ በመፍታት ቀሪ ስራዎችን ሙሉ በሙሉ
ለማሳካት ዝርዝር አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ሲሉ አቶ እያሱ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *