መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2014-“መንግስት የተወሰኑ ግለሰቦችን ክስ ማቋረጡ ዘላቂ አገራዊ ጥቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።” ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ

መንግስት የተወሰኑ ግለሰቦችን ክስ ማቋረጡ ዘላቂ አገራዊ ጥቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

መንግስት ለያዘው አገራዊ ምክክርና ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል።

ይህንን አገራዊ አንድነት ለማምጣትም ብዙ ተከታይ ያላቸውን እስረኞች ክስ ማቋረጥ ማስፈለጉን ነው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተናገሩት።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት፣ የተመቻቸ ፖለቲካዊ ሁኔታን ለመዘርጋት፣ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ ለመገንባት ያለመ ነው ውሳኔው።ይህ ውሳኔው በየደረጃው የሚመለከተው አካል ተወያይቶበት የወሰነው ሲሆን ዘላቂውን የሀገር ጥቅም ከግምት ያስገባም መሆኑንነው ሚንስትሩ ያነሱት።

መንግስት የእነዚህን ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ ሲያደርግ ግለሰቦቹ ለአገራዊ መግባባት ያላቸውን ሚናም አምኖበት ስለሆነ ለሰላማዊ ምክክር የተሰጣቸውን እድል እንዲጠቀሙበትም ጥሪ ቀርቦላቸዋል ማለታቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።

ሚንስትሩ በሌላኛው መግለጫቸው ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና መስመራዊ መኮንኖች የተሰጠውን የማዕረግ እድገትና የጀግና ሜዳሊያ ሽልማትን አንስተዋል።

ሽልማቱ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ሊታደጉ በመቻላቸው የተሰጠ እና በቀጣይም አገሪቱን የሚታደግ መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት እንዲችሉ አቅም የሚፈጥር ነው ሲሉ አስረድተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *