መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2014-ሰሜን ኮርያ በኪም ጆንግ ኡን ክትትል ስር አዲስ ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ማሰወንጨፏን ይፋ አደረገች

ሰሜን ኮርያ በመሪዋ ኪም ጆንግ ኡን ክትትል ስር አዲስ ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ አድርጌያለሁ ስትል አስታውቃለች።የመንግስት የዜና ወኪል የሆነው ኬሲኤንኤ እንዳስታወቀው በትላንትናው እለት የተወነጨፈው ሚሳኤል 1000 ኪ.ሜ ርቀት በመጓዝ ኢላማውን መምታቱን ዘግቧል።

ሰሜን ኮርያ ለሶስተኛ ጊዜ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ያደረገች ሲሆን ከባልስቲክ ሚሳኤል የበለጠ ለእይታ አዳጋች መሆኑም ተነግሮለታል።ኪም በአዲስ ዓመት ንግግራቸው የሀገራቸውን የመከላከያ አቅም ለማጠናከር ቃል ከገቡ በኃላ ሁለቱ ሙከራዎች በአንድ ሳምንት ተከናውነዋል።

ሰሜን ኮሪያ ትላንትና ጠዋት ባልስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ አስታዉቀው የነበረ ቢሆንም ፒዮንግያንግ ግን ሙከራዬ ሀይፐርሶኒክ ነው ስትል ተናግራለች፡፡ሰሜን ኮርያ ሙከራ መፈጸሟን በጃፓን የባህር ዳርቻ ጠባቂዎችም ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ባለስቲክ ሚሳኤል የመሰለ ነገር መተኮሱን ተናግረው ነበር፡፡በቶኪዮ የሚገኘው የመንግስት የዜና ኤጀንሲ የኪዮዶ በሙከራዉ ዙሪያ ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ማስወንጨፏን መቀጠሏ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡አስቸኳይ ስብሰባ ያካሄደው የደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሙከራዉ ማዘኑን ገልጿል ሲል የፕሬዚዳንቱ ሰማያዊ ሀውስ አስታዉቋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *