መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2014-በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ባለፉት ስድስት ወራት በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የ62 ሰዎች ህይወት አልፏል

በአዲስ አበባ ከተማ እና ዙሪያዋ ባለፉት ስድስት ወራት በድንገተኛ አደጋዎች የ62 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 112 ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ከብስራ ሬድዮ ጋር በነበራው የስልክ ቆይታ እንደተናገሩት በስድስት ወራት ውስጥ 236 ድንገተኛ አደጋዎች ደርሰዋል ብለዋል።

ከአደጋዎቹ መካከል 136 የእሳት ቃጠሎ ሲሆኑ 100 አደጋዎች ደግሞ ከእሳት ውጪ የደረሱ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡በ2014 ዓ.ም በግማሽ ዓመት ከደረሰው አደጋ በእሳት ቃጠሎ የ5 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች 57 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በአካል ላይ በደረሰ አደጋ በእሳት 54 ሰዎች ላይ በድንገተኛ አደጋዎች ደግሞ 58 ሰዎች ቆስለዋል። በደረሱት አደጋዎች ከ62 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረትም መውደሙ ተነግሯል፡፡እንደ አቶ ንጋቱ ማብራሪያ በተያዘው የበጀት ዓመት በስድስት ወራት የደረሱት አደጋዎች ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በሞት ሆነ በንብረት ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በስድስት ወራት 46 ሰዎች ህይወት ሲልፍ በዘንድሮው አስራ ስድስት በመጨመር ስልሳ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።የአደጋዎች መንስኤ በተመልከተ ከ236 አደጋዎች የ101 አደጋዎች መንስኤ የታወቀ ሲሆን የ135 አደጋዎች መንስኤ አለመታወቁን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ በከተማ ከእሳት አደጋ ውጪ የደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የሚባሉት የኤሌክትሪክ ፣ኩሬ ውስጥ እና ክፍቱን በተተዉ ቦታዎች ላይ መግባት እና የጎርፍ አደጋዎች መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *