መደበኛ ያልሆነ

ጥር 4፤2014-ቨርቿል ሪያሊቲ የተሰኘውን መነፅር የሚያደርጉ ላሞች የሚሰጡት ወተት በቀን 5 ሊትር ጨምሯል

የቱርክ ገበሬዎች የላሞችን የቀን የወተት ምርት ለመጨመር ሱ ከብቶች በበጋ ወቅት አረንጓዴ ግጦሽ ውስጥ እንዳሉ እንዲመስላቸው የሚያደርግ Virtual Reality የተሰኘ መነፅር እንዲጠቀሙ አድርገዋል።ይህንን መነፅር ለላሞቻቸው የተጠቀሙት የኢዝዜት ኮካክ ቤተሰብ እንደሚለው ከመነፅሩ በተጨማሪ ድምፅ እንዲሰሙ እና ዘና እንዲሉ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ እንደሚገጠምላቸው ተናግሯል።

ላሞቹ ከጨላለመ በኃላ እንኳን በፀሀይ የግጦሽ መስክ ውስጥ እንዳሉ መነፅር ያሳምናቸዋል ተብሏል።በዚህ ቴክኖሎጂ የተነሳ በቀን 22 ሊትር ወተት ይሰጡ የነበሩ ላሞች ወደ 27 ሊትር ከፍ እንዲል አድርጓል።

መነፅሩ ላሞቹ ዘና እንዲሉ ማድረግ መቻሉን እና ጥራት ያለው ወተት እንዲሰጡ ጭምር አግዟል።በሩሲያ ይህ ቴክኖሎጂ ከዚህ ቀደም ተሞክሮ ነበር።

የኮካክ ቤተሰብ ለጊዜው አስር መነፅር ግዢ የፈፀመ ሲሆን 180 መነፅሮችን ለመግዛት እቅድ መያዙን አስታውቋል።የላሞቹን ባህሪና ስሜት የሚተነትን ቺፕ በእግራቸው ላይም ተገጥሞላቸዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *