መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2014-ህብረት ባንክ በ2.8 ቢሊዮን ብር ያስገነባወን ህንጻ ቅዳሜ ያስመርቃል

ከተቋቋመ ሃያ ሶስት አመታትን ያስቆጠረው ህብረት ባንክ 3,300 ካ.ሜ ላይ ያረፈውን እና በ2.8 ቢሊዮን ብር ያስገነባውን ህንጻ ቅዳሜ እንደሚያስመርቅ የህብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት መላኩ ከበደ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ህብረት ባንክ አዲስ ያስገነባውን ባለ 37 ወለል ህንጻ ህብር ታወር በሚል ስያሜ ቅዳሜ የሚያስመርቅ ሲሆን የህንጻው ግንባታ ከስድስት ዓመት በፊት የተጀመረ ሲሆን በኮቪድ ምክንያት ግንባታው በተወሰነ ደረጃ የዘገየ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግንባታውን አጠናቅቆ ስራ ጀምሯል።

ህንጻው ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቁ ዘመናዊ ፋሲሊቲዎችን ያሉት ሲሆን በኮምፓስ የሚሰሩ 13 አሳንሰሮች፣ በሴንተር የሚሰራ መብራት እና ውሃ ከ147 በላይ ካሜራዎች፣ባለ 270 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ ስክሪን በአጠቃላይ ሁለገብ እና የተሟላ አና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ህንጻ መሆኑ ተገልጾል።

ህብረት ባንክ ከዚህ በፊት የዋና መስሪያ ቤት ስራውን በሶስት የተለያዩ ቦታዎች ከፋፍሎ ይሰራ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት አዲስ ባስገነባው ዘመናዊ ህንጻ በአንድ ቦታ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ለደንበኞች ሆነ ለሰራተኞች ምቹ የሆነ የአሰራር ሂደት መፍጠሩን ገልጿጻ።

አዲሱ ህንጻ ስራ በመጀመሩ ከዚህ በፊት ለሶስት መስሪያ ቤቶች ኪራይ ይወጣ የነበረውን 1.5 ሚሊዮን ብር ማትረፍ እንደሚቻልም የህብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት መላኩ ከበደ ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *