መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2014-ግድቡን ስንሞላ ሲያስፈራሩን ነበር ግን ምንም አላመጡም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት ሳምንታዊ በፖለቲካ፣ በዲፕሎማሲ፣በኢኮኖሚክ ዲሎማሲ እና በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ረገድ ማብራያ ሰጥተዋል። ካነሷቸው ነጥቦች መካከል በዋናነት በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁነት ስለመቀየሩ በመግለፅ በጦርነቱ ጊዜ ከነበረው የፖለቲካ አንድምታ አንጻር ሲታይ መቀየሩን መገንዘብ እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።

አሸባሪው ቡድን አዲስ አበባ ለመግባት መቃረቡን ሲነገር ነበር፣አዲስ አበባ አውሮፕላን ለማሳረፍ የሚያስችል ደህንነት የላትም፣ ዜጎቻቸውን ከፍለው ሲያስወጡ የነበሩ ሃገራት እንደነበሩ የሚታወስ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ይህ አልፎ አሁን ላይ ሁሉ ነገር መቀየሩ የፖለቲካው ሁነት መለወጡን ያሳያል ብለዋል።

አሸባሪው ቡድን ወደነበረበት ተመልሷል ወይ ተብሎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ “አዎ ወደ ነበረበት ተመልሷል ቦታውን አስለቅቀናል ይህ ደግሞ ወደ ቦታው መመለሱን ያሳያል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በአባይ ግድብ ዙሪያ የመጀመሪያው ዙር ኃይል የሚያመነጭበት ጊዜ በመቃረብ ላይ ነው፤ ቀኑ ባይታወቅም መቃረቡን ግን መናገር እንችለን ድርድሩ ግን አይቆምም ሲሉ አምባሳደር ዲና መናገራቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።ግድቡን ስንሞላ ሲያስፈራሩን ነበር፤ ግን ምንም አላመጡም ደግሞም ምንም አያመጡም ይልቁኑ ለሱዳን ጠቃሚ ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ጨምረው ተናግረዋል።

ቤተልሄምእሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *