የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት በስድስት ወራት ውስጥ 198ሺ ከረጢት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ 189 ሺ የደም ከረጢት መሰብሰቡን በብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ዘርፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተመስገን አበጀ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
የተሰበሰው ደም በኢትዮጰያ በሚገኙ 40 የደም ባንኮች የተሰበሰበ ሲሆን በአዲስ አበባ ብቻ ከ6ሺ 166 በላይ ደም እንደተሰበሰበ ተገልጿል፡፡
ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር በዘንድሮ ዓመት ከፍተኛ ደም እንደተሰበሰ የተገለፀ ሲሆን ፡ባለፉት ስድስት ወራት የደም እጥረት ያልነበረበት ወር እንደነበር ተገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደም ብስራት ሬዲዮ የኔጌቲቨ የደም ዓነቶች እጥረት ማጋጠሙም እንደዘገበ የሚታወስ ሲሆን አሁንም ግን እጥረቱ በከፊል እንደተቀረፈ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የደም ለጋሾች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነ እና ይህም የደም እጥረት እንዲያጋጥም ሊያደርግ እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በቀይ መስቀል ጊቢ ፣በጤና ጥበቃ ጎማ ቁጠባ እና በሾላ ገበያ ጤና ጣቢያ ጊቢ ውስጥ ፣ በመገኘት ደም ቢለግስ ሲሉ ዶ/ር ተመስገን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሳምራዊት ስዩም