መደበኛ ያልሆነ

ጥር 6፤2014-በናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቡሃሪ የተጭበረበረ ፊርማ ሲንቀሳቀስ የነበር ሀሰተኛ የጦር ጄኔራል ተያዘ

የናይጄሪያውን ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪን ፊርማ በማጭበርበር ወንጀል ፈጽሟል የተባለ አንድ የሀሰት ጦር ጄኔራል በቁጥጥር ስር ውሏል።የናይጄሪያ ኢኮኖሚ እና ፋይናንሺያል ወንጀሎች ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ እንደ ጦር ጄኔራል በመምሰል ከ650 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ሃብት ሲያጭበረብር የነበረዉ ግለሰብ ኦሉዋሴጉን እንደሚባል ይፋ አድርጓል፡፡

የናይጄሪያ ኢኮኖሚ እና ፋይናንሺያል ወንጀሎች ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ ተጠርጣሪው በፕሬዚዳንቱ ሹመት ለማግኘት እንደታጨ እና የተወሰነ ጉቦ ከሰጠ እንደሚሾም በመግለጽ ለጉቦ የሚሆነዉን ገንዘብ ለመክፈል እንደሚያስፈልገው በመናገር ሲያጭበረብር ነበር ተብሏል፡፡

ኦሉዋሴጉን ስለ ታሰረበት ምክንያት ምንም ያልተናገረ ሲሆን ኮሚሽኑ ግን ምርመራውን ሲያጠናቅቅ በህግ እንደሚጠይቀዉ አስታዉቋል፡፡በሌጎስ በሚገኘዉ መኖሪያ ቤቱ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የጦር መሳሪያ እና በርካታ ሀሰተኛ ሰነዶች ተገኝቷል፡፡ተጠርጣሪው ለማጭበርበር የፕሬዚዳንቱ ፊርማ ያለበትና የናይጄሪያ ጦር ሃይል አዛዥ እንደሆነ አስመስሎ ሲንቀሳቀስ ነበር ተብሏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *