መደበኛ ያልሆነ

ጥር 6፤2014-በአዲስ አበባ በመጀመሪያው ስድስት ወራት በቀን በአማካይ ለ2.5 ሚሊዮን ህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ተሰጥቷል ተባለ

በአዲስ አበባ ከተማ በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት በቀን በአማካይ ለ2.5 ሚሊዮን ህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠቱን የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ አስታዉቋል፡፡በአዲስ አበባ በ387 የጉዞ መስመር ላይ በየቀኑ በአማካይ 3 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ከቦታ ቦታ እንዲጓጓዝ ለማድረግ ታቅዶ 2.5 ሚሊዮን ማጓጓዝ የተቻለ ሲሆን፥ ከዕቅድ አኳያ 83 በመቶ ማሳካት መቻሉን በትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ 541 ሺህ 200 ተጠቃሚ በየቀኑ ለማጓጓዝ ታቅዶ 510 ሺህ 40 እንዲጓጓዝ በማድረግ የዕቅዱን 94 በመቶ ማሳካት እንደቻለ ተነስቷል፡፡በሸገር የብዙሃን መደበኛ ትራንስፖርት 310 ሺህ 310 በየቀኑ ለማጓጓዝ ታቅዶ በ13 ጊዜ ነጠላ ጉዞ ስሌት 227 ሺህ 500 ህዝብ ወይም የዕቅዱን 73 በመቶ መሸፈን መቻሉን ተጠቁማል፡፡

በተያያዘ በሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡስ 290 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎችን በየቀኑ ለማጓጓዝ ታቅዶ በ11 ጊዜ ነጠላ ጉዞ ስሌት 150 ሺህ በላይ ማጓጓዝ ችሏል፡፡ በኮድ 3 ድጋፍ ሰጪ ታክሲዎች 996 ሺህ 744 በየቀኑ ለማጓጓዝ ታቅዶ በ 7 ጊዜ ደርሶ መልስ ስሌት 831 ሺህ 600 ህዝብ እንዲጓጓዝ ተደርጓል፤ ከአፈጻጸም አኳያ 83 በመቶ የተሳካ እንደነበር አቶ አረጋዊ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በኮድ 1 ታክሲዎች ፣በሀይገር ሚድባስ፣ በአይሱዙ ቅጥቅጥ እና በፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡስ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ተገልጿል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *