መደበኛ ያልሆነ

ጥር 6፤2014-የባልደራስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አፋር ገቡ !!

በቅርብ ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የመጀመሪያውን ጉዞ ወደ አፋር በዛሬው ዕለት አደረጉ።

የፓርቲው ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ ፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ የፋይናንስ ሃላፊ ወ/ሪት ዘቢባ ኢብራሂም እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ወግደረስ ጤናው ወደ አፋር ተጉዘዋል።

በአፋር ለአንድ ቀን በሚያደርጉት ቆይታ በዋናነት በግንባር ከፍተኛ ተጋድሎ ላደረጉት እና አያደረጉ ላሉ የቁርጥ ቀን ኢትዮጵያዊያን ልጆች ምስጋና ያቀርባሉ።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን እና ከአሸባሪው የህውሃት ኃይል ጋር ፊት ለፊት እየተፋለሙ ላሉት የወገን ጦር አባላት አስመልክቶ “እንደ አቅሜ ፤ ድጋፍ ለሀገሬ !” እኔ እያለሁ ወገኔ አይደፈርም ፤ አይራብም ፤ አይሰደድም ! በሚል መርህ ቃል ያሰባሰባው ድጋፍ ካደረገባቸው ቦታዎች ፤ በጭፍራ አካባቢ ላሉ ተፋናቃዮች እና ለአፋር ልዩ ኃይል መሆኑ የሚታወስ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *