መደበኛ ያልሆነ

ጥር 12፤2014-ጫማ ሰርቀሻል በሚል ምክኒያት የቤት ሰራተኛቸዉን ቢላ በማጋል ጉዳት ያደረሱ ጥንዶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

በሆሳዕና ከተማ ሴች ዱና ቀበሌ በትዳር ተጣምረው የሚኖሩት ጥንዶች ማሞ ሀይሉ እና አበባየሁ ሀንዴቦ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጫማ ሰርቀሻል በሚል ምክኒያት የቤት ሰራተኛቸዉ የሆነችዉን ማርታ ሱሊቶ ቢላ በማጋል ሰዉነቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የሆሳዕና ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዋና ኢ/ር ካሳ ሊሊሶ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

ወንጀሉ የተፈጸመው ጥር 4 2014 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ጫማ ሰርቀሻል በሚል ምከንያት ጥንዶቹ የቤት ሰራተኛቸዉን ቢላ በእሳት በማጋል በሰዉነቷ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተጠቁሟል ። በእለቱ ጥቆማ የደረሰዉ የሆሳዕና ከተማ ፖሊስ በቦታዉ በመገኘት ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አዉሏል።

በተበዳይ ላይ የደረሰዉ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ወደ ወላይታ ሶዶ ሆስፒታል ለተጨማሪ ህክምና መላኳን ኢ/ር ካሳ ሊሊሶ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *