መደበኛ ያልሆነ

ጥር 13፤2014-የሱዳን ጦር አዛዥ በሀገሪቱ ተቃውሞ ቢቀጥልም አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾሙ

የሱዳን ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል አብደልፈታህ አል ቡርሃን ለመሰረተዉ አዲስ መንግስት 15 ሚኒስትሮችን መሾሙን አስታወቀ፡፡|እርምጃው በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን ከተቆጣጠረ ከሶስት ወራት በኋላ ሲሆን ይህም በምርጫ ሊደረግ የታቀደውን ሽግግር ውድቅ ያደረገ መሆኑን ማሳያ ነዉ ተብሏል፡፡

መፈንቅለ መንግስቱ ከተጀመረ ወዲህ ከ70 በላይ ሰልፈኞች በጸጥታ ሃይሎች የተገደሉበት ከፍተኛ ተቃውሞ ተካሂዷል።ዘጋቢዎች እንደሚሉት አዲስ መንግስት መሰየሙ ወታደራዊ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን እንዲለቅ የሚፈልጉ ተቃዋሚዎች ዉሳኔዉ የሚያስከፋ ሆኗል፡፡

ቀደም ሲል በሱዳን የሚገኙ ዳኞች ተቃውሞውን በሃይል ለማፈን በሚል የተፈጸሙ ወንጀሎችን እንዲመረምር ጠይቀው ወታደራዊ መሪዎች መከላከያ በሌላቸው ተቃዋሚዎች ላይ አሰቃቂ ጥሰቶችን ፈፅመዋል ሲሉ ከሰዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ብጥብጥ እስካልቆመ እና በሲቪል የሚመራ መንግስት እስካልተመለሰ ድረስ ለሱዳን የኢኮኖሚ ድጋፏን እንደማትቀጥል ገልጻለች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *