መደበኛ ያልሆነ

ጥር 16፤2014-በህንድ ብድር ተከልክያለዉ ያለዉ ግለሰብ የባንኩን ቅርንጫፍን በእሳት አቃጠለ

የ33 አመቱ ህንዳዊዉ ሰዉ ዋሲም ሙላ የሚባል ሲሆን የበጎ አድራጎት ሰራተኛ ነዉ፡፡በመንግስት ከሚመራው ካናራ ባንክ ታህሳስ ወር ላይ 1.6 ሚሊየን ሩፒ (21,600 ዶላር) ብድር ይጠይቃል። ማመልከቻው በባንኩ ውድቅ የተደረገበት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የባንኩን የብድር ፖሊሲ የሚያሟላ አይደለም በሚል ነበር።

በዚህ የተበሳጨዉ ዋሲም በሞተር ሳይክሉ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ተቀጣጣይ ፈሳሽ በማርከፍከፍ ቅርንጫፍ ባንኩ እንዲቃጠል አድርጓል፡፡የዓይን እማኞች ከተቃጠለው ሕንፃ ላይ ከፍተኛ ጭስ ሲወጣ በመመለከት ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን ዋሲም በአካባቢው ሰዎች ተይዞ ፖሊሶች እስኪደርሱ ድረስ እንዲቆይ ተደርጓል።
ዋሲም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ይመራ የነበረ ሲሆን ለስራዉ ማስፋፊያ የማሽን ግዢ ለመፈጸም ፈልጎ ለ1.6 ሚሊዮን ሩፒ ብድር ማመልከቱን ለሌሎች ሲፈቀድ እኔ ተከለከልኩኝ ሲል ለፖሊስ ተናግሯል፡፡እንደ እድል ሆኖ በቃጠሎም ምንም ዓይነት ገንዘብ ሆነ ወርቅ ወይም ሌላ ውድ ነገር አልወደመም።

የእሳት አደጋ ተከላካዮች እሳቱን በተሳካ ሁኔታ ለማጥፋት ቢችሉም 1.2 ሚሊዮን ሩፒ ዋጋ ያላቸው አምስት ኮምፒውተሮች፣የባንክ ደብተር ማተሚያ ማሽን፣የገንዘብ ቆጠራ ማሽኖች እና አሌክትሪክ መስመሮች መዉደማቸዉን ፖሊስ አስታውቋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *