መደበኛ ያልሆነ

ጥር 20፤2014-ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከአሳ ምርት የዉጪ ንግድ ዝቅተኛ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

በተያዘዉ 2014 ዓመት ከአሳ ንግድ የዉጪ ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸምን ለማስመዝገብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ባለፉት ስድስት ወራት ከታቀደው በታች ዝቅተኛ ውጤት መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታዉቋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደበሌ ለማ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት‹ኢትዮጵያ አብዛኛውን የአሳ ምርት ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን የምትልክ በመሆኗ በሁለቱ ሃገራት መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ችግር ሳቢያ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ ሊሆን እንደቻለ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ይህ ችግር ሲቀረፍ ምርቱን ወደ ውጪ ሃገራት በመላክ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማድረግ ጥረት ይደረጋል ሲሉ የገለጹት አቶ ደበሌ እንደ አጠቃላይ ሲታይም በዘርፉ የምርት መጠን ማነስ የሚስተዋል በመሆኑም በዚሁ ስራ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩን አያይዘው ጠቁመዋል፡፡

ዘርፉ በሚያስገኘው ጥቅም ልክም ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ምርቱን ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ያሉት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ ከተፈጥሮ አሳ ማስገር ወደ ዘመናዊ እርባታ ስርአት ሽግግር አለመኖሩ ለችግሩ አንደኛው መንስኤ ሆኗል፡፡ይህንን ችግር ለመቅረፍና እንደ ሌሎች ዘርፎች የአሳ ምርት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ለኢትዮጵያ እንዲያበረክት በቀጣይ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ለመተግበር መታቀዱ ተገልጿል፡፡

ቅድስት ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *