መደበኛ ያልሆነ

ጥር 23፣2014-በሱዳን የጸጥታ ሀይሎች በሰልፈኞች ላይ በወሰዱት እርምጃ 1 ሰው ተገደለ

የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች በዋና ከተማዋ ካርቱም ውስጥ በፀረ መፈንቅለ መንግስት ሰልፎች ላይ በወሰዱት እርምጃ የ27 ዓመት እድሜ ያለውን ሰልፈኛን መግደላቸውን የህክምና ባለሙያዎች ቡድን ዘግቧል።

የሱዳን ዶክተሮች ማእከላዊ ኮሚቴ በትናንትናዉ እለት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈረው መልዕክት “መሀመድ የሱፍ ኢስማኢል በካርቱም በተካሄደው የዲሞክራሲ ሰልፍ ላይ በፀጥታ ሀይሎች በተፈጸመ ጥቃት መገደሉን ይፋ አድርጓል፡፡

በደረቱ ላይ በጥይት መመታቱን የሱዳን ዶክተሮች ማእከላዊ ኮሚቴ ቢያሳውቅም የጉዳቱ ዓይነተቱ ገና አልታወቀም ብሏል፡፡የትናንትናው በጸጥታ አካላት የደረሰዉን ጥቃት ተከትሎ ከጥቅምት ወር ጀምሮ በፀረ መፈንቅለ መንግስት ተቃውሞ በሱዳን የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር 79 ደርሷል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በትናንትናዉ እለት በካርቱም እና በሌሎች ከተሞች ጎዳናዎች ላይ የጥቅምት ወር ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣን በማዉገዝ የዲሞክራሲ ሽግግርን እንዲደረግ እና ሙሉ የሲቪል መንግስት እንዲመሰረት ጠይቀዋል። መፈንቅለ መንግስቱ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ለሶስት አስርት አመታት ከአለም አቀፍ መገለል በኋላ ሱዳን ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር የምታደርገውን ሽግግር ያሻሽላል የሚለዉን ተስፋ ላይ ስጋት ደቅኗል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *