መደበኛ ያልሆነ

ጥር 24፣2014-በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዲጂታል ትምህርት ቤት ተመረቀ

በኤግልላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ ስር ከሚተዳደሩት ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ስኩል ኦፍ ክላውድ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል ትምህርት ቤት ይፋ አድርጓል።የዲጂታል ትምህርት ቤቱ ራስን ለማስተማር የሚረዱ በታዋቂ እና ስኬታማማ በሆኑ ግለሰቦች የተዘጋጁ መማሪያ ቪዲዮችን ማካተቱን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

የኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት በርሱፈቃድ ጌታቸው እንደተናገሩት የዲጂታል መማሪያው መከፈት የትምህርት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጥቅም ያለው መሆኑን በመግለፅ ለተጠቃሚዎች ክፍት የተደረጉት የግል ዕውቀትን የሚያሳድጉ ቪዲዮች ናቸው ብለዋል። በመቀጠል የዲጂታል ትምህርት ቤቱ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ ቪዲዮዎች እንደሚኖረው አክለዋል።

የዲጂታል ትምህርት ቤቱ ላይ ለመመዝገብ ተጠቃሚዎች የድርጅቱን ድሕረ-ገፅ መጠቀም የሚችሉ ሲሆን የተዘጋጁት መማሪያዎችም በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡ ናቸው። በቅርቡ በዝግጅት ላይ ባለው የድርጅቱ መተግበሪያ ላይ ተጠቃሚዎች በመመዝገብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ መተግበሪያ ክፍያ መፈፀም እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ዛሬ ለሕዝብ ክፍት በሆነው የዲጂታል ትምህርት ቤት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው የታዋቂው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ኤርሚያስ አመልጋ ማስተር ክላስ ትምህርቶች ሲሆኑ የመማሪያ ቪዲዮዎች ተጠቃሚዎች ማየት ይችላሉ ተብሏል።

ስኩል ኦፍ ክላውድ የኤግል ቴክኖሎጂ ስር ከሚተዳደሩት ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሲሆን ደንበኞች ከፍለው በኦንላይን መማር እንዲችሉ እና ራሳቸውን ማስተማር እንዲችሉ የሚያደረገው የኩባንያው ዲጂታል ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ቀዳሚ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *