
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሩስያ እና የአሜሪካ ልዑካን መካከል ግጭት የተፈጠረ ሲሆን ጉባኤው በዋሽንግተን ጠሪነት በዩክሬን ድንበር ላይ ስላለው የሞስኮን ጦር ሃይልን በተመለከተ ነበር።የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዳለ እናምነለን ነገር ግን ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች አሜሪካ ቆራጥ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቀዋል።
ውጤቱም አሰቃቂ ይሆናል ብለዋል። በአውሮጻ ውስጥ በአስርተ አመታት ውስጥ ትልቁ የወታደር ኃይል መሰባሰብ እንዳለም አምባሳደሯ ተናግረዋል። የሩሲያ አቻቸው በበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስ በሞስኮ ጉዳዮች ላይ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃገብነት እየፈፀመች ነው ሲሉ ከሰዋል።
አሜሪካ እና እንግሊዝ ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጥሉ በምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል። በፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዛ እንደተናገሩት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እቅድ አላት መባሉን ማረጋገጫ የሌለው መረጃ ሲሉ አጣጥለውታል።
የሰራዊት ግንባታዋን በታመለከተ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተረጋገጠ አይደለም ብለዋል።ሩሲያ ወታደሮቿን በግዛቷ ውስጥ ማሰማራቷ የዋሽንግተን ጉዳይ እንዳልሆነም ተናግረዋል።
በስምኦን ደረጄ