መደበኛ ያልሆነ

ጥር 24፣2014-ኬንያ በግድያ ወንጀል የሚጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦችን ለብሪታኒያ አሳልፋ ሰጠች

ኬንያ በግድያ ወንጀል የሚፈለጉ ሁለት የብሪታኒያ ዜጎችን ለእንግሊዝ አሳልፋ መስጠቷ ተሰምቷል። ግለሰቦቹ ባለፈው ሳምንት በቁጥጥር ስር የዋሉት በናይሮቢ ዋና የገበያ ማዕከል በሆነ ኪሊማኒ አካባቢ ነው እንደሆነ የኬንያ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

የኬንያ ፖሊስ እንዳስታወቀው እ.ኤ.አ በ2019 በለንደን ከተማ አሌክስ ስሚዝ የሚባል የ16 አመት ታዳጊ በስለት ወግቶ በመግደል በተጠርጣሪዎቹ ላይ አለም አቀፍ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው ነበር። የዩናይትድ ኪንግደም ሜትሮፖሊታን ፖሊስ በበኩሉ ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች አንዱ የስለት ጥቃቱን መፈፀሙን አስታውቋል።

ሌላኛው ተጠርጣሪ ወንጀሉ ሲፈፀም ከተሰረቁት ሁለት መኪኖች በአንዱ ላይ ተሳፍሮ ነበር ተብሏል። ሌሎች ሁለት ሰዎች በግድያው ላይ በነበራቸው ተሳትፎ በእንግሊዝ በቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *