መደበኛ ያልሆነ

ጥር 25፣2014-በከባድ ራስ ምታት ለ20 ዓመታት ያህል ሲሰቃይ የነበረው ወጣት በልጅነቱ መናገር የፈራው ጥይት በራስ ቅሉ ውስጥ እንደነበር ተነገረ

ዢኦ ቼን የተባለዉ የ28 አመቱ ቻይናዊዉ ወጣት በራስ ምታት ለዓመታት ሲሰቃይ ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ህመሙ እየጠነከሩ ይመጣል። ቼን ህመሙ የተከሰተው በሳምንቱ ቀናት በቂ እንቅልፍ በማጣቴ ነው ብሎ አስቦ የነበረ ቢሆንም ብዙ መተኛት መፍትሄ አላመጣለትም፡፡

በሼንዘን ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደረገለት የኤምአርአይ ምርመራ በዢኦ ቼን ራስ ቅል በግራ በኩል አንድ እንግዳ ነገር ይገኛል። በተደረገዉ ምርመራ ጥይት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ስለ ሁኔታዉ ያስታዉስ እንደሆነ ለቼን በቀረበለት ጥያቄ መሰረት የ8 አመት ልጅ እያለው እኔ እና ወንድሜ በቤት ውስጥ በሽጉጥ ስንጫወት ድንገት ተተኩሶ በጥይት መመታቱን ተናግሯል።

እኔ እና ወንድሜ በወላጆቻችን እንዳንሰደብ ፈርተን ነበር፤ ብዙ ደም ስላልፈሰሰኝና ቁስሉም በፀጉሬ ተሸፍኖ ስለነበር ቤተሰቦቼ ሳያዩት እኔ በጊዜ ሂደት ረሳሁት ሲል ተናግሯል፡፡በተደረገለት ህክምና ጥይቱ የወጣ ሲሆን በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *