መደበኛ ያልሆነ

ጥር 25፣2014-በጊኒ ቢሳው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን ተከትሎ በርካቶች ሰዎች መገደላቸዉ ተሰማ

በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጊኒ ቢሳው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን ተከትሎ በርካታ የጸጥታ ሃይሎችን መገደላቸዉን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ሁኔታው በቁጥጥር ስር መዋሉን በመግለጽ “በዲሞክራሲ ላይ ያልተሳካ ጥቃት” ሲሉ ድርጊቱን ጠርተውታል።

በዋና ከተማው ቢሳው ፕሬዝዳንቱ በካቢኔ ስብሰባ ላይ በነበሩበት ጊዜ በሚገኝ የመንግስት ህንጻ አቅራቢያ የተኩስ እሩምታ መከፈቱ ተነግሯል፡፡ወታደሮቹ ፕሬዚዳንቱን እና ሚኒስትሮቹን አግተዉ ስለመቆየታቸዉ ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢምባሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኑኖ ጎሜዝ ናቢያም ጋር እየመከሩ ባለበት ወቅት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በቤተመንግስቱ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸዉን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።የምዕራብ አፍሪካ ክልላዊ መሪዎች ድርጊቱ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መሆኑን ገልጸው ወታደሮቹ ወደ ጦር ሰፈር እንዲመለሱ አሳስበዋል።

የተፈጠረዉ ነገር ግልፅ ያልተደረገ ሲሆን ታጣቂዎቹ እነማን እንደነበሩ እስካሁን አለመታወቁና እና ፕሬዚዳንቱም ስለተገደሉት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ከዓለም ድሃ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው የቀድሞዋ የፖርቹጋል ቅኝ ተገዢ ጊኒ ቢሳዉ ከ1980 ጀምሮ ዘጠኝ የመፈንቅለ መንግሥት ግልበጣና ሙከራ ተፈጽሞባታል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *