መደበኛ ያልሆነ

ጥር 25፣2014-አሜሪካ ሩሲያን ወደ ጦርነት ዉስጥ ለመክተት እየሞከረች ነው ሲሉ ፑቲን ተናገሩ

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩናይትድ ስቴትስ ሀገራቸውን በዩክሬን ጦርነት ውስጥ እንድትገባ እየሞከረች ነው ሲሉ ከሰዋል። ለበርካታ ሳምንታት በዘለቀዉ ዉጥረት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት የሰጡት ፑቲን እንደተናገሩት የአሜሪካ አላማ ግጭትን እንደ ምክንያት በመጠቀም በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ለመጣል ነው ብለዋል ።

በተጨማሪም በአውሮፓ ውስጥ የኔቶ ጥምረት ኃይሎች መጨመርን በተመለከተ ሩሲያ ያላትን ስጋት ዋሽንግተን ችላ ትላለች ሲሉም ተናግረዋል።በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ የሩስያ ወታደሮች መስፈር ውጥረት እንዲነግስ ምክንያት ሆኗል፡፡

ሩሲያ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ወደ 100,000 የሚጠጉ ወታደሮቿን ከታንክ፣ እስከ አየር ሀይል ድረስ ወደ ዩክሬን ድንበር አስጠግታለች፡፡ነገር ግን ሩሲያ የዩክሬይን ደቡባዊ ግዛት የነበረችዉን የክራይሚያ ልሳነ ምድር ወደ ራሷ ከቀላቀለች እና በምስራቅ ዶንባስ አካባቢ የተካሄደውን ደም አፋሳሽ አመፅ ከደገፈች ከስምንት አመታት በኃላ ወረራ ለማድረግ አቅዳለች በሚል ከምዕራባውያን የሚቀርበዉን ውንጀላ ውድቅ ታደርጋለች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *