መደበኛ ያልሆነ

ጥር 26፣2014-በጊኒ ቢሳው ባልተሳካው መፈንቅለ መንግስት 11 ሰዎች መገደላቸዉ ተረጋገጠ፤ የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ በአደንዛዥ ቡድን ሳይቀራ እንዳልቀረ ተነግሯል

ማክሰኞ እለት በተቃጣው እና በከሸፈዉ የፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎን የመንግስት ግልበጣ ሙከራ 11 ሰዎች መሞታቸውን የጊኒ ቢሳው መንግስት አስታዉቋል። ህይወታቸዉን ያጡት ወታደሮች ጨምሮ ሲቪሎች እንደሚገኙበት ተነግሯል።

የመንግስት ግልበጣ ሙከራዉን አድርገዋል የተባሉትን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎችን ለማግኘት ከፍተኛ ምርመራ ተጀምሯል።ሰራዊቱ ከተቃጣዉ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ በኃላ በዋና ከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ጥበቃ እያደረገ ይገኛል፡፡

ሱቆች እና ባንኮች በድጋሚ እየተከፈቱ ቢሆንም በቢሳው ከተማ ገበያዎች ጥቂት ደንበኞች ብቻ ወዉጣታቸዉ ተነግሯል፡፡በቤተመንግስቱ አቅራቢያ ለአምስት ሰዓታት ያህል የተኩስ ልውውጥ የተደረገበት አካባቢ እስካሁን ለእንቅስቃሴ ዝግ ተደርጓል፡፡

ጊኒ ቢሳው በላቲን አሜሪካ እና አውሮጳ መካከል ለሚደረገዉ የአደንዣዥ እጽ የኮኬይን ዝውውር ማዕከል በመሆኗ በርካቶች የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ የአደንዛዥ ዕፅ ቡድን ሊመራዉ እንደሚችል ግምታቸዉን እያስቀመጡ ይገኛል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *