መደበኛ ያልሆነ

ጥር 26፣2014-የፌስቡክ ዕለታዊ ተጠቃሚዎች ቁጥር በ18 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀነሱ ተነገረ

ግዙፉ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ በ18 ዓመታት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የእለት ተእለት ንቁ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ቀንሷል፡፡ፌስቡክን ጨምሮ በርካታ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮችን የያዘውሜታ ኔትወርክ እንዳስታወቀዉ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ ባሉት ሶስት ወራት የተጠቃሚዎቹ ቁጥር ካለፈው ሩብ አመት ከነበረበት 1.93 ቢሊዮን ተጠቃሚዎች ጋር ሲነጻጸር ወደ 1.929 ቢሊዮን ዝቅ ብሏል፡፡

ኩባንያዉ እንደ ቲክ ቶክ እና ዩቲዩብ ካሉ ተቀናቃኞች በሚያደርጉት ውድድር የገቢ እድገትን እንደሚቀንስ አስጠንቅቋል፡፡የሜታ አክሲዮኖች በኒውዮርክ ከ20 በመቶ በላይ ቀንሷል።ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ በተለይም ወጣት ተጠቃሚዎች ወደ ተቀናቃኝ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ፊታቸዉን በማዞራቸዉ የፌስቡን የሽያጭ እድገት መጎዳቱን ተናግረዋል፡፡

ፌስቡክ በ18 ዓመት ታሪኩ ዉስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕለታዊ ተጠቃሚዎች የቀነሰ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት ግማሽ ሚሊዮን ገደማ ተጠቃሚዎችን አጥቷል፡፡የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በአብላጫዉ የቀነሰዉ በአፍሪካ እና በላቲን አሜሪካ ሀገራት ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *