መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 1፤2014-በአፋር ክልል ከወደሙ የጤና ተቋማት ዉስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት ዳግም ወደ ስራ መመለሳቸዉ ተነገረ

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀዉ የህወሓት ቡድን በአፋር ክልል ውስጥ በወረራ በቆዩባቸው ጊዜያት ከ74 በላይ የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን ከነዚህ ከወደሙ ተቋማት ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት ዳግም ወደ ስራ መግባታቸውን የአፋር ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ መሀመድ ኡመር ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ እንደተናገሩት በክልሉ በወራሪው ሀይል ከወደሙት የጤና ተቋማት ውስጥ አስር የጤና ጣቢያዎች እና አስር የጤና ኬላዎች መልሶ የማቋቋም ስራ ስላልተሰራባቸው አገልግሎት እየሰጡ እንደማይገኝ አንስተዋል።

የጤና ተቋማቱን መልሶ በማቋቋም ሂደት ላይ ያሉበት ቦታ ገጠራማ እና ለትራንስፖርትም አመቺ አለመሆናቸዉ በተጨማሪም ድጋፍ ለማድረግ የአቅም ውስንነት መኖሩ ስራዉ ፈታኝ እንዳደረገዉ አቶ መሀመድ አንስተዋል፡፡

የአፋር ክልልን የጤና ሥርዓትን ለማቋቋም እና መሣሪያ ለማሟላት ከ20 ዓመት በላይ እንደወሰደ የተነገረ ሲሆን የህውሀት ቡድን ግን ለመዝረፍ እና ከጥቅም ውጪ ለማድረግ የፈጀበት ግዜ አጭር መሆኑን ባለሙያዉ ጠቁመዋል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *