መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 1፤2014-ታጣቂዎች በጊኒ ቢሳው ሬዲዮ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመፈጸም አነጣጥረዋል መባሉን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጠረ

በጊኒ ቢሳው ዋና ከተማ የተሰማው ከባድ የተኩስ ድምጽ ከአንድ ሳምንት በፊት ከተደረገዉ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በኋላ በአንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች ላይ ሽብር መፍጠሩ ተሰምቷል፡፡ባልታወቁ ታጣቂዎች የተፈፀመው ጥቃት በመንግስት ህንጻዎች ላይ ሳይሆን በአንድ የግል ሬዲዮ ጣቢያ ላይ ቢሆንም በመንግስት ሰራተኞች ላይ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡

የካፒታል ሬድዮ የስርጭት ማስተላለፊያ መሳሪያዎች እና ኮምፒውተሮችን በጥቃቱ ወድመዋል።ጣብያው ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ (ቪኦኤ) ጋር ተባባሪ ሲሆን ጥቃቱን ማን እና ለምን እንደፈፀመ ግን ግልጽ አይደለም::ይኸው የሬዲዮ ጣቢያ ቀደም ሲል በጁላይ 2020 ላይ ኢላማ ተደርጎ ነበር።ከባድ የጥይት ድምጽ ከሰሙ በኋላ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች ወደ የቤታቸው ሲሸሹ ታይተዋል።

ባለፈው ማክሰኞ ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎን ከስልጣን ለመገልበጥ ሲሞክሩ ቢያንስ 11 ሰዎች መገደላቸዉን የመንግስት ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።ፕሬዚዳንቱ የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ በጊኒ ቢሳዉ አልተደረገም ከላቲን አሜሪካ ሀገራት ወደ አዉሮጳ የአደንዛዣ እጽ ንግድ የሚዘዉሩ የወንጀለኛ ቡድኖች ሴራ ነዉ ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *