
የኬንያ የትምህርት ሚኒስትር አካላዊ ቅጣት በሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች እንደታገደ በማስታወስ ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ መምህራን እጃቸዉን ከማንሳት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡ሚኒስትር ጆርጅ ማጎሃ በኬንያ ድንበራማ አካባቢዎችን በጎበኙበት ወቅት ተማሪዎችን ሲደበድቡ የተያዙ መምህራን በህጉ መሰረት እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩን ይህንን አስተያየት የሰጡት በአካባቢው አንድ ተማሪ አምስት ቂጣ በልቷል በሚል ከባድ የአካላዊ ቅጣት ከተፈጸመበት ከቀናት በኋላ ነው።ይህዉ ተማሪ ቅጣቱን ተከትሎ በኩላሊቱ እና በብልቱ ላይ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ገብቷል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር እና ሌሎች መምህራን በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡በአካባቢዉ የሚገኙ የትምህርት ኃላፊዎች ትምህርት ቤቱን ምዝገባ ያላከናዉ እና የንጽህና ችግር እንዳሉበት ባደረጉት ፍተሻ አረጋግጠዋል፡፡ሚኒስትሬ ማጎሃ ለህግ የተገዢነት ችግር ያለባቸው ትምህርት ቤቶች እንደሚዘጉ እና ተማሪዎች ወደ አጎራባች ትምህርት ቤቶች እንደሚላኩ ተናግረዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ