መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 1፤2014-“ፐልፕ” ያመረቱ ተማሪዎች የ245ሺ ብር አሸናፊ ሆኑ

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምህንድስና ሴት ተማሪዎች የፍራፍሬ እና ሌሎች የዕፀዋት ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም ለወረቀት መስሪያ የሚሆን “ፐልፕ” በማምረት በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ የ245 ሺህ ብር አሸነፊ ሆኑ፡፡

ተማሪዎቹ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የማይመረተውን ፐልፕ የተሰኘውን ለወረቀት ማምረት ስራ የሚውል ግብዓት በማምረታቸው ነው ውድድሩን ያሸነፉት፡፡የተማሪዎቹ የፈጠራ ስራ ፕሮጀክት በገንዘብ ቢደገፍና ወደ ተግባር ቢለወጥ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ከሚሰጠው ፋይዳ በተጨማሪ፥ የአከባቢ ንፅህናን በመጠበቅ ደረጃ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ወረቀት ለማምረት የሚቆረጡ ዛፎችን ቁጥር በመቀነስ በአለም ሙቀት መጨመር ላይ የሚደርሰውን አሉታዊ ተጽዕኖ በመቆጣጠር ደረጃ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል መባሉን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ተረፈ-ምርቶችንና የሚወገዱ ቆሻሻዎችን በመጠቀም የሚሰሩ ምርቶች ለተጠቃሚዎች በአነስተኛና በዝቅተኛ ዋጋ ስለሚቀርቡ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይኖረዋልም ተብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *