መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 2፤2014-ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች በኤሌክትሪክ ሀይል መሰረተ ልማት ላይ ያደረሰዉን ጉዳት ለመተካት ከ23 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የህወኃት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በኤሌክትሪክ ሀይል መሰረተ ልማት ላይ ያደረሰዉን ጉዳት መልሶ ለመተካት ከ 23 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልገዉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን እንዳስታወቁት ህወሓት በሁለቱ ክልሎች ላይ ያደረሰዉ የመሰረተ ልማት ዉድመት ሰፊ እንደነበር መናገራቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

ቡድኑ ባደረሰዉ ውድመት እና ዝርፊያም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ከ 1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበትም አስታዉቀዋል ። እንደ አቶ ሞገስ መኮንን ማብራሪያም ይህን ዉድመት ለመተካት ከ 23 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *