መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 2፤2014-አሜሪካ በሶማሊያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ እገዳን ጣለች

አሜሪካ የዲሞክራሲ ሂደትን በማናጋት በተከሰሱ የሶማሊያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ገደቦችን ጥላለች።ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ ተዓማኒነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ ስትገፋፋ ብትቆይም ምርጫዉ በጊዜዉ ማካሄድ ግን አልተቻለም፡፡

የአሜሪካ መንግስት ባወጣዉ መግለጫ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የቪዛ እገዳው በወቅቱ እና ግልጽ ምርጫን ተግባራዊ ለማድረግ ያላባቸዉን ግዴታ ባልተወጡ ባለስልጣናት ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም ጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ባነጣጠረ መልኩ በማዋከብ፣ በማስፈራራት፣ እስር የፈጸሙ ባለስልጣናት የቪዛ እገዳዉ ተግባራዊ ይሆንባቸዋል፡፡

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ስልጣን ባለፈው አመት የካቲት ወር የተጠናቀቀ ቢሆንም ምርጫው ተረዝሟል፡፡ቀጥተኛ የህዝብ ተሳትፎ የማይደረግበት የፓርላማ ምርጫ በህዳር ወር ተጀምሮ እስከ ታህሳስ 24 ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም በተፈጠረዉ ዉዝግብ ምክንያት ዘግይቷል፡፡

ምርጫው እስከ የካቲት 25 ቀን እንዲጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ እና የክልል አመራሮች ጥር 9 ቀን ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።የዩናይትድ ስቴትስ የስቴት ዲፓርትመንት የፖለቲካ መሪዎቹ ሂደቱን በጊዜ ገደብ መሰረት ለማጠናቀቅ የገቡትን ቃል መከተል አለባቸው ብሏል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *