መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 2፤2014-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ህንጻ 48ኛ ወለል ለህዝብ ክፍት ይደረጋል ተባለ

የፊታችን እሁድ የሚመረቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ህንጻ 48ኛ ወለል ለህብረተሰብ ክፍት እንደሚደረግ ባንኩ አስታውቋል፡፡በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አዲሱ ህንጻ ምርቃት እና 80ኛ ዓመት ምስረታ ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የህንፃው የመጨረሻው 48ኛ ወለል አዲስ አበባ እና አካባቢዋን ለመመልከት በሚያስችል መልኩ ሆኖ ከዘመናዊ የሬስቶራንት አገልግሎት ጋር መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ይህ በባንኩ የተዘጋጀው 48ኛ ወለል ለአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና የቱሪስት መስህብ የሚሆኑ መዳረሻ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።የህንጻው ምድረ ግቢም ለሁሉም ህብረተሰብ ክፍት ሆኖ በቀላሉ የሚታዩ ማረፊያ የተሰናዳላቸው እንዲሁም በልዩ ልዩ ሀገር በቀል እጽዋት፣ የውሃ ፋውንቴን እና የቅርጻ ቅርስ ስራዎች ያሸበረቁ ናቸው ብለዋል።

የህንጻው ገጽታ የአፍሪካ አልማዝ ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ሲሆን በግንባታው ከስምንት ሀገራት የተውጣጡ 28 ታዋቂ የግንባታ እቃ አቅራቢዎች እንደተሳተፉበት ብስራት ሬድዮ ከባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ሰምቷል።

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አንባሳደር አካባቢ በ303 ሚሊየን አምስት መቶ ሺ ዶላር ያስገነባውን ባለ 53 ወለል ህንፃ የፊታችን እሁድ ያስመርቃል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *